

አዲስ አበባ ፣ሚያዝያ 16 ፣2017 ሩስ አፋሪክ (RussAfrik)
በሩሲያና በአፋሪካ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፎረም ከማዝያ 14-15 /2017 በአዲስ አበባ ተደረገ።
በሩስያ እና አፍሪካ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ፎረም ጋዜጠኞችና የሚዲያ ባለሙያዎች ከሩሲያ ና ከተለያዮ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሳተፍበት ለ2ቀናት የተደረገው ስብሰባ በ “የወዳጅነት እና ትብብር መንገድ” የሚል መሪ ሀሳብ ተካሂዷል ።
በመክፈቻ ስነ-ስረአቱ ላይ ንግግር ካቀረቡት ታዋቂ ሰዎች መካከል ፦
ቫሌሪያያድሮቭስካያ ALPHA-DIALOGUE ማዕከል ውስጥ የህዝብ ግንኙነት ምክትል ዳይሬክተር
ከሩሲያ።
ማሪና ቦግዳኖቫ ALPHA-DIALOGUE የትምህርት ስራዎች ምክትል ዳይሬክተር
ከሩሲያ።
ኖቪኮቭ አሌክሳንደር ዲሚትሪቪች በአፍሪካ ምርምር ማዕከል የሳይንስ አካዳሚ የፕሮጀክት ማኔጅር በጎርቻኮቭ ፈንድ እና የምርምር ባለሙያ
ከሩሲያ።
አቶ ተዋህደ በላቸው በልሁ
ሪሶርስ ኢንደስትሪ ኤንድ ትሬዲንግ ፒኤልሲ ዋና ስራ አስኪያጅ
ከኢትዮጵያ ።
አሌክሴይ ሉክያንኮ የአፍሪካ አገሮች ጋር የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበር,
የፕሮጀክት ቢሮ ሃላፊ
ከሩስያ።
ሰርጌይ ጋላኒን የIMBRICS ፎረም አማካሪ
ከሩሲያ ።
ቪክቶሪያ ቡዳኖቫ Sputnik Africa የአፍሪካ ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ
ከሩሲያ ።
በስብሰባው ላይ ብዙ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በተለይ አቶ ሲምብ ኤሚል ፓርፋይ፣ የግሎባል LTV ዋና ስራ አስኪያጅ፣ አፍሪካዊ ሚዲያዎች የሚጋፈጧቸውን ተግዳሮቶች አንስተዋል አቅርበዋል። እነዚህም አነስተኛ ሀብቶች፣ አስተማማኝ የመረጃ ምንጮች አለማግኝት እና የውሸት ዜናዎች መበራከትን ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ናቸው ።
በነዚህም ነጥቦች በመድረኩ ላይ ጋዜጠኞች የየሀገራቸውን ተሞክሮዎች እያቀረቡ ክርክሮችም ተደርጎባቸዋል።
የፓን-አፍሪካ ጋዜጠኞችም የአንድነት ጥሪ አቅርበዋል
ጋዜጠኞቹም ከአፍሪካ ከጋና፣ ጊኒ-ኮንአክሪ፣ ካሜሩን፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ኢትዮጵያ እና ሌሎች አገሮች የተውጣጡ ጋዜጠኞች ተገኝተው ልምድ ተለዋውጠዋል ። ይህም የሙያዊ ክህሎቶችን ማጠናከር እና የምንጮችን ማረጋገጫ ማሻሻል ላይ አፅንኦት ተሰጥቷል። ፎረሙ በጋዜጠኞች መካከል የተቀናጀ ትብብር ለመፍጠር የጋራ ቁርጠኝነት እንደሚኖር ተገልጿል። ይህም አስተማማኝ ይዘት እና መረጃን ለማካፈል ያስችላል ተብሏል።
ስብሰባው ሲጠናቀቅ ለሁሉም ተሳታፊዎች የተሳታፊነት የምስክር ወረቀት የተሠጠ ሲሆን በቀጣይ ይህንን መሠል ስብሰባ እና የሩሲያንና የአፍሪካን የሚዲያ ባለሙያዎችን ህብረት በሚያጠናክር መልኩ በሌላ የአፍሪካ ሀገር እንደሚደረግ ተገልጿል ።

